አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቦንጋ እና ቴፒ ከተሞች ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ የለውጡን ትሩፋቶች የሚዘክር ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የድጋፍ ሰልፉ በለውጡ መንግሥት የተገኙ የመጋቢት 24 ድሎችንና ሁለንተናዊ ለውጦችን የሚዘክር እንዲሁም ለተመዘገቡ ስኬቶች እውቅና የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የተመዘገቡ ለውጦችን የሚገልጹ የተለያዩ መልዕክቶች በሰልፈኞቹ እየተላለፉ መሆናቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
የሰልፉ ተሳታፊዎች በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ላሉ የልማት ሥራዎች እውቅና በመስጠት በቀጣይም የተገኘው ልማት እንዲቀጥል ከለውጡ ከመንግሥት ጎን መሆኑን አመልክተዋል።
በሰልፎቹ ላይ የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።