የሀገር ውስጥ ዜና

ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አቀረቡ

By Adimasu Aragawu

April 07, 2026

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦላቸው በውጤቶቹ ላይ ግምገማ እና ውይይት መደረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።