አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፓሪስ ኦሎምፒክ 200 ሜትር ሻምፒዮኗ አትሌት ጋቢ ቶማስ በአዲስ አበባ ግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ አሳውቃለች።
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደው የአንድ ቀን ዓለም አቀፍ ውድድር ሚያዚያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ አሜሪካዊቷ አትሌት ጋቢ ቶማስ እንደምትሳተፍ ተረጋግጧል፡፡
ጋቢ በፈረንጆቹ 2024 በፓሪስ ኦሎምፒክ በ200 ሜትር የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ስትሆን÷ ከቡድን አጋሮቿ ጋር ደግሞ የወርቅ ሜዳልያ ለሀገሯ ማስገኘቷ ይታወሳል።
አትሌቷ በቡዳፔስት የብር ሜዳልያ፣ በቶኪዮ ዓለም ሻምፒዮና ደግሞ የነሐስ ሜዳልያ አሸናፊ መሆኗ ይታወቃል፡፡