አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በአምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ሕልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የኀዘን መልዕክት÷ አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል ነው ያሉት።
በዲፕሎማሲው መስክ ለሀገራቸው ኢትዮጵያና ለአፍሪካ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ፣ አስተምህሮና ብልህ አመራር ምንጊዜም ይታወሳሉ ብለዋል።
አምባሳደር ቆንጂት ትጉህና ከብረት የጠነከሩ ዲፕሎማት እንደነበሩም አስታውሰዋል።