አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቡሩንዲ ፕሬዚዳንትና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ኢትዮጵያና ቡሩንዲ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ሲሆኑ÷ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን በማቋቋም በተለያዩ መስኮች ትብብራቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ።
ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።