የሀገር ውስጥ ዜና

ፀሎተ ሐሙስ በተለያዩ መንፈሳዊ ክንውኖች እየተካሄደ ነው

By Adimasu Aragawu

April 09, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፀሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የሃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

የሰሙነ ሕማማት 4ኛ ቀን የሆነው ፀሎተ ሐሙስ በዛሬው ዕለት በቤተክርስቲያኗ አድባራትና ገዳማት በማለዳ ኪዳን፣ በስግደት፣ በሕፅበት እግር፣ በቅዳሴና ሌሎችም መንፈሳዊ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።

ዕለቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻውን እራት የበላበት እና እግራቸውን በትሕትና ያጠበበት ነው፡፡