አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፀሎተ ሐሙስ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቱን ተከትሎ እየተካሄደ ይገኛል።
በቤተክርስቲያኗ ልደታ ማርያም ካቴድራል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየተከበረ በሚገኘው መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ሊቀጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሐነኢየሱስን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ በዚህ ወቅት÷ ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትሕትናን ያስተማረበትን አርዓያ በመከተል የምእመናንን እግር አጥበዋል።
ፀሎተ ሐሙስ የተቸገሩ የሚረዱበት፣ የታመሙ የሚጎበኙበት እንዲሁም የትሕትና እና የፍቅር ዕለት መሆኑን ገልጸው÷ ይህን ተግባር ወደ ዕለት ተዕለት ሕይወታችን በማምጣት ከወገኖቻችን ጋር በመተጋገዝ መኖር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።