ስፓርት

ሀድያ ሆሳዕና አርባ ምንጭ ከተማን አሸነፈ

By Yonas Getnet

April 09, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና አርባ ምንጭ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ የሀድያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ግብ ሄኖክ አርፍጮ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል።

ቀደም ብሎ በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ ሀዋሳ ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ነገሌ አርሲ እና ኢትዮጵያ መድን 1 አቻ ተለያይተዋል፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ከ12 ሰዓት ጀምሮ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ወላይታ ድቻ ጨዋታቸውን እያደረጉ ናቸው።