የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራረሙ

By Yonas Getnet

April 09, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ታድመዋል።

ሁለቱ ሀገራት በመከላከያ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በውሃና ኢነርጂ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በዲጂታል መታወቂያ እና በቱሪዝም ዘርፎች መፈራረማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

እነዚህ ሁሉን አቀፍ ስምምነቶች ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ መሆናቸው ተገልጿል።

የመግባቢያ ስምምነቶቹ የሁለቱን ሀገራት ሰፊ አቅም በመደመር ወደ ብልጽግና ለምናደርገው የጋራ ጉዞ መሠረት የሚጥሉ ናቸው ሲልም ጽሕፈት ቤቱ አስረድቷል።