የሀገር ውስጥ ዜና

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከቡሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት ጋር ተወያዩ

By sosina alemayehu

April 10, 2026

‎አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከቡሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት አንጀሊን ንድያይሺሚዬ ጋር ተወያይተዋል።

‎ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ የቡሩንዲ ቀዳማዊት እመቤት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት በብሔራዊ ቤተመንግስት ተቀብዬ ጉብኝት አድርገናል ብለዋል። ‎ በነበረን ቆይታም በምንሰራቸው የጋራ ስራዎች እና የቀጣይ ትብብሮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ነበረን ሲሉ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።