የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By sosina alemayehu

April 10, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬ በኢትዮጵያ ያደረጉትን የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ እንዳመለከተው፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቡሩንዲውን ፕሬዚዳንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬን ሸኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ፕሬዚዳንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬ ከሁለት ቀናት ይፋዊ ጉብኝታቸው በኋላ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት መሸኝታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ጠቁሟል።