የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የስቅለት በዓል እየታሰበ ነው

By Mikias Ayele

April 10, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል እየታሰበ ነው።

በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች እየተነበቡ ሲሆን፥ ዕለቱ ስቅለት ፍቅር፣ ይቅር ባይነትና ትሕትና በተግባር የተገለጠበት መሆኑ ተገልጿል።

የቤተክርስቲያኗ አባቶች የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት አስተምህሮ ፍቅር፣ ይቅር ባይነትና ትሕትናን በተግባር የተገለጠበት ዕለት እንደሆነም ተናግረዋል።

ቤተክርስቲያኗ ዕለቱን በስግደት፣ በጾምና ፀሎት ሥነ-ስርዓት የምታስበው ክርስቶስ ለሰው ልጆች ነፃ መውጣት የከፈለውን ዋጋ በማሰብ እንደሆነ ተመላክቷል።

የክርስቶስ መስቀል ፍቅር፣ አንድነትና ይቅር ባይነት የተገለጠበት መሆኑን በማንሳት÷ ከክርስቶስ ፍቅርን እና ፍጹም ይቅር ባይነትን የምንማርበት የድህነት ቀን ነው ብለዋል።

የመፋቀር፣ መተሳሰብ እና የአብሮነትን ተምሳሌት ማድረግ እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት፡፡