አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ክልሎች በመዘዋወር ከፖለቲካ ፓርቲዎች እና የክልል የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል።
በውይይቱ ፓርቲዎች በቅደመ ምርጫ ሂደት ላይ ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች በተመለከተ ምክክር ተደርጓል፡፡
በተመሳሳይ ከክልል የስራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ሥርጭትን አስመልክቶ ሊቀርብ ስለሚገባው ተሽከርካሪ እና የነዳጅ ሁኔታ በተመለከተ ምክክር ተደርጓል፡፡
የቦርዱ አመራሮቹ በክልሎቹ በነበራቸው ቆይታ በምርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውረው የመራጮች ምዝገባ ሂደትን መመልከታቸውን የቦርዱ መረጃ ያመላክታል፡፡