የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የስቅለት በዓል ተከበረ

By Mikias Ayele

April 10, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል ተከብሯል።

በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች የተነበቡ ሲሆን፥ ዕለቱ ስቅለት ፍቅር፣ ይቅር ባይነትና ትሕትና በተግባር የተገለጠበት መሆኑ ተገልጿል።

የቤተክርስቲያኗ አባቶች የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት አስተምህሮ ፍቅር፣ ይቅር ባይነትና ትሕትናን በተግባር የተገለጠበት ዕለት እንደሆነም ትምህርተ ወንጌል ሰጥተዋል።

ቤተክርስቲያኗ ዕለቱን በስግደት፣ በጾምና ፀሎት ሥነ ሥርዓት የምታስበው ክርስቶስ ለሰው ልጆች ነፃ መውጣት የከፈለውን ዋጋ በማሰብ እንደሆነ ተመላክቷል።

የቤተክርስቲያኗ አባቶች የክርስቶስ መስቀል ፍቅር፣ አንድነትና ይቅር ባይነት የተገለጠበት መሆኑን በማንሳት÷ ከክርስቶስ ፍቅርን እና ፍጹም ይቅር ባይነትን የምንማርበት የመዳን ቀን ነው ብለዋል።

የመፋቀር፣ መተሳሰብ እና የአብሮነትን ተምሳሌት ማድረግ እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት፡፡