የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Adimasu Aragawu

April 11, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኢሎምቢ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ የአፍሪኤግዚም ባንክ ፕሬዚዳንት የሆኑትን ጆርጅ ኢሎምቢን (ዶ/ር) ዛሬ ተቀብያለሁ ብለዋል።

በነበራቸው የጋራ ቆይታም ስትራቴጂካዊ ግንኙነታችንን በምናጠናክርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገናል ነው ያሉት።