ዓለምአቀፋዊ ዜና

ዓለም ተስፋ የጣለበት የአሜሪካና ኢራን የሰላም ውይይት በፓኪስታን እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

April 11, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ እና ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረውን ጦርነት ለማስቆም በፓኪስታን ኢስላማባድ የገጽ ለገጽ የሰላም ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

በተጠባቂው የሰላም ውይይት ከአሜሪካ በኩል በምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ የተመራ ልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

በኢራን በኩል ደግሞ በሀገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባዔ ሞሐማድ ባገር ጋሊባፍ የተመራ ልዑክ መሳተፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በፓኪስታን አደራዳሪነት እየተካሄደ የሚገኘው የሰላም ውይይት በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረውን አውዳሚ ጦርነት ለማስቆም ያለመ ነው፡፡

ከዚህ ባለፈም የሀገራቱ የፊት ለፊት የሰላም ውይይት በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አንደሚኖረው ነው የተገለጸው፡፡

የኢስላማባዱ ታሪካዊ የሰላም ውይይት አሜሪካ እና ኢራን ከ47 ዓመታት በኋላ ፊት ለፊት የተገናኙበት መድረክ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

የአሜሪካ እና ኢራን የሰላም ውይይት ተሳታፊዎች ከተጠባቂው ድርድር አስቀድሞ ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሸህባዝ ሸሪፍ ጋር የተናጠል ውይይት አድርገዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ