አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ምሽት 12 ሰዓት 30 ላይ ማንቼስተር ሲቲን ያስተናግዳል፡፡
በሊጉ 61 ነጥብ በመሰብሰብ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ማንቼስተር ሲቲ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 6 ዝቅ ለማድረግ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
ያለፉትን ሁለት ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎች አቻ የተለያየው ማንቼስተር ሲቲ ወደ ድል ለመመለስ የሚያደርገው ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት እየተፋለመ የሚገኘው ቼልሲ በጨዋታው ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ባለሜዳው ቡድን ቼልሲ በሊጉ ከተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ድል አልባ ጉዞ በኋላ ወደ ድል ለመመለስ ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
በሌላ የሊጉ ጨዋታዎች ኖቲንግሀም ፎረስት ከአስቶንቪላ፣ ሰንደርላንድ ከቶተንሃም ሆትስፐር እንዲሁም ክሪስታል ፓላስ ከኒውካስል ዩናይትድ በተመሳሳይ ቀን 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡