ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ…

By Adimasu Aragawu

April 13, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ በኦልድትራፎርድ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሊድስ ዩናይትድን ያስተናግዳል።

ሊጉ ለሀገራት ጨዋታ ከመቋረጡ በፊት የመጨረሻ መርሐ ግብሩን በአቻ ውጤት ያጠናቀቀው ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ድል ለመመለስ ከበርካታ ቀናት በኋላ ወደ ሜዳ ይገባል።

ያለፉትን አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሊጉ ማሸነፍ ያልቻለው ተጋጣሚው ሊድስ ዩናይትድ በበኩሉ÷ ወደ አሸናፊነት ለመምጣት ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ሁለቱን ሲያሸንፍ በሦስቱ አቻ ተለያይተዋል።

ትናንት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ ቼልሲን 3 ለ 0፣ ሰንደርላንድ ቶተንሃም ሆትስፐርን 1 ለ 0፣ ክሪስታል ፓላስ ኒውካስል ዩናይትድን 2 ለ 1 ሲያሸንፉ፣ አስቶን ቪላ ከኖቲንግሀም ፎረስት 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት መለያየታቸው ይታወቃል።

ሊጉን አርሰናል በ70 ነጥብ ሲመራው ማንቼስተር ሲቲ በ6 ነጥብ ዝቅ ብሎ ይከተላል።

ማንቼስተር ዩናይትድ በ55 ነጥብ 3ኛ እንዲሁም አስቶንቪላ በተመሳሳይ 55 ነጥብ በግብ ክፍያ አንሶ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በወንድማገኝ ጸጋዬ