አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ራንገል ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ የፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ፓውሎ ራንገልን አግኝቼ፤ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን እና ቀጣይ ትብብሮችን በምናጠናክርባቸው ቁልፍ መስኮች ዙሪያ መክረናል ብለዋል።