አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አትሌቲክስ የአንድ ቀን የሩጫ ውድድር ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ታስተናግዳለች።
በውድድሩ ከ70 በላይ ስመጥር የዓለም አቀፍ አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን÷ ኹነቱ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ያላትን የቆየ ዝና በውድድር አዘጋጅነትም ጭምር የምታሳይበት ነው።
መንግሥት ለስፖርት ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ሰፋፊ መሰረተ ልማቶች ተገንበተዋል፤ በዚህም የዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ውድድሮች ትኩረት ኢትዮጵያን ማድረግ ጀምረዋል።
አዲስ አበባም እንግዶቿን ተቀብላ ውድድሩን ለማስተናገድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቋን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።
በውድድሩ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት ታዋቂ አትሌቶች አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን÷ የፓሪስ ኦሊምፒክ ሻምፒዮኗ አትሌት ጋቢ ቶማስ እንዲሁም አሜሪካውያን አትሌቶች ክርስቶፈር እና ሻንቴል ቀድመው ከገቡ አትሌቶች መካከል ይጠቀሳሉ።