ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም የንግድ መርከቦች ክፍት ሆነ

By Mikias Ayele

April 17, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእስራኤልና ሊባኖስ መካከል የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ የሆርሙዝ ወሽመጥ ለሁሉም የንግድ መርከቦች ክፍት መሆኑን ኢራን አስታውቃለች፡፡

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ እንዳሉት ÷ የተኩስ አቁም ስምምነቱ እየተተገበረ ባለበት ጊዜ ውስጥ ማንኛውም የንግድ መርከብ በሆርሙዝ ወሽመጥ ማለፍ ይችላል።

ኢራን ወሳኝ የነዳጅ መተላለፊያ መስመር የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ መክፈቷን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ በ11 በመቶ ዝቅ ማለቱን ሲ ኤን ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

እስራኤል እና ሊባኖስ በአሜሪካ አሸማጋይነት በተደረገው ድርድር የ10 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወቃል፡፡

በእስራኤል፣ አሜሪካ እና ኢራን መካከል ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ ንግግሮች እየተደረጉ እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ሙሉ በሙሉ ክፍት ማድረጓን ገልፀው፤ ለውሳኔው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሚኪያስ አየለ