አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የክፍያ ስርዓቱን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ሊያደርግ ነው አሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አካሉ አሰፋ።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ የከተማ አውቶቡስ የስምሪት እና ቁጥጥር ስርዓቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቢሆንም የክፍያ ስርዓቱ ግን በወረቀት የሚከናወን ነው።
በዚህም የክፍያ ስርዓት በኢ-ቲኬቲንግ ቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግ በመንግሥት እና የግል አጋርነት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የክፍያ ስርዓቱ በስማርት ካርድ፣ ኪው አር ኮድ፣ ቴሌ ብር እንዲሁም ሁሉም ባንኮች እንደሚከናወንም የገለጹት።
እየለማ ያለው የቴክኖሎጂ ስርዓት የሁሉንም ባንኮች መጠቀም የሚያስችል ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ÷ ቀስ በቀስ ሁሉም የክፍያ ስርዓቶች ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል።
በዚህም የኢ-ቲኬቲንግ የሙከራ ስራ መጀመሩንና አብዛኛዎቹ ስራዎች መጠናቀቁን አመልክተዋል።
በመሳፍንት እያዩ