ስፓርት

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

By Adimasu Aragawu

April 20, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 29ኛው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ በጉባኤው መክፈቻ ላይ አዲሱ የፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ በአንድ ዓመት ውስጥ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን አንስተዋል፡፡

የአትሌቲክሱን ዘርፍ ለማሳደግ ፌዴሬሽኑ ከመንግስት ጋር በመተባበር የውድድር ዝግጀት እና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግ ጥረት ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚህ መድረክ በ28ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለጉባኤ፣ በ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ በውጭ ኦዲት ሪፖርት፣ በ2018 በጀት ዓመት የሥራ እቅድና በጀት፣ በተቋማዊ አሰራር ሪፎርም ሰነድ እና የሰው ኃይል መዋቅራዊ ጥናት ቀርቦ ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።

እንዲሁም በተሻሻለው የፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ፣ በአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ እና በተሻሻለውን የፌዴሬሽኑ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር መመሪያ በአጀንዳነት የሚመከርባቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተገልጿል።

በሌዊ በለጠ