አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከኦስትሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቤአተ ሜይንል-ራይዚንገር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና የኦስትሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
በተጨማሪም በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ምክክር ማድረጋቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።
በሀገራቱ መካከል ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ጠንካራ ግንኙነት ያለ ሲሆን፤ ትምህርት፣ ሳይንስና ኢኮኖሚን ጨምሮ በተለያዩ የልማት ትብብር መስኮች በአጋርነት ይሰራሉ።