የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ሕብረት መካከል ያለው ግንኙነት እየተጠናከረ መጥቷል – ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

April 20, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ሕብረት መካከል ያለው ግንኙነት እየተጠናከረ መጥቷል አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)።

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የአውሮፓ ሕብረት ዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ጆሴፍ ሰኪላን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት÷ ዛሬ የተጀመረው የአውሮፓ ሕብረት-ኢትዮጵያ ቢዝነስ ፎረም ውጤታማ መሆኑ አስደሳች መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ እና በሕብረቱ መካከል ያለው ግንኙነት እየተጠናከረ መምጣቱን በማንሳት÷ የታዳሽ ኃይልን ጨምሮ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚደረገው ትብብር የበለጠ ሊጠናከር ይገባል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

ኮሚሽነር ጆሴፍ ሰኪላ በበኩላቸው÷ በታዳሽ ኃይል መሠረተ ልማት፣ በዲጂታይዜሽን እና ሌሎች የትብብር መስኮች ሕብረቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።