አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከባንግላዲሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካሊሉር ራህማን (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ታዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በኢትዮጵያ እና ባንግላዲሽ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር ተወያይተናል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ እና የሀገራቱን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡