አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀረሪ ክልል በሁሉም ዘርፎች እየተከናወኑ የሚገኙ ውጤታማ ስራዎችን ለማስቀጠል ይሰራል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ።
በክልሉ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ይገኛል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ ግምገማው በአፈፃፀም ረገድ የታዩ ውስንነቶችን በመለየት በቀሪ ወራት ለማረምና ስኬቶችንም ለማስቀጠል ያግዛል።
በመሆኑም በክልሉ ቱሪዝም፣ ኢንቨስትመንትና ሌሎች ዘርፎች ለክልሉ ኢኮኖሚ እድገት እያበረከቱ የሚገኘውን አስተዋጽኦ መመልከት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማጎልበት ረገድም የተሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ነው ያሉት።
የሕግ የበላይነትን ከማረጋገጥ እንዲሁም ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን ከማስወገድ አንጻር የተከናወኑ ተግባራትን በጥልቀት መመልከት እንደሚገባም ገልጸዋል።
በክልሉ ሰው ተኮር የሆኑ በጎ አድራጎት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።
በተስፋዬ ኃይሉ