የሀገር ውስጥ ዜና

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Adimasu Aragawu

April 24, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤስፒን ቤርዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጌዲዮን (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ ሊተባበሩባቸው የሚችሉባቸው ብዙ መስኮች እንዳሉ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እና ኖርዌይ መካከል ዘርፈ ብዙ ትብብር ሊኖር እንደሚገባ ገልጸው÷ ግንኙነታቸውም ጠንካራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ትብብር በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በአካባቢ ጥበቃ ሊሰፋ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ኤስፒን ቤርዝ በበኩላቸው÷ የተለያዩ የኖርዌይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያለውን ዕድል መጠቀም ይፈልጋሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ የኮፕ32 አዘጋጅ በመሆኗ ሀገራቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግም ማረጋገጣቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመልክቷል፡፡

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በኦስሎ ቆይታቸው ከኖርዌይ የዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር፣ ከአየር ንብርትና አካባቢ ሚኒስትር፣ ከኢንቨስትመንት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር፣ ከልማት ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና ከባለሃብቶች ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ መስኮች ዙሪያ መክረዋል።