አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማረሚያ ቤቶች ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር በተሰሩ ስራዎች የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው አለ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን።
20ኛው የፌዴራል እና የክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነሮች የጋራ ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽነር ጄኔራል የኑስ ሙሉ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ፈጣን ለውጥ ከታየባቸው ተቋማት መካከል ማረሚያ ቤቶች ግንባር ቀደም ናቸው።
በፌዴራል እና በክልል ማረሚያ ቤቶች ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመተግበርና ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር በተሰሩ ስራዎች የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዚህም በጎ ልምዶችን ለማስተግበር የማረሚያ ተቋም አመራርና ሰራተኞችን እንዲሁም የሕግ ታራሚዎችን በዕውቀትና በክህሎት ማልማት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
በማረሚያ ተቋማት የማረምና ማነፅ ስራዎችን፣ የሰው ሃብት አስተዳደርን፣ ትምህርትን እና ጤናን በቴክኖሎጂ በማዘመን ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራርን መዘርጋት ለነገ የማይባል እንደሆነም አስረድተዋል።
በተቋማቱ የተመዘገቡ ውጤቶችና የተጀመሩ መልካም ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።
በስመኝ ስዩም