ስፓርት

ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 3 ለ 1 አሸነፈ

By Melaku Gedif

April 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር ዛሬ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 3 ለ 1 አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ኦካይ ጁል፣ ቢኒያም ጌታቸውና ዘላለም አባተ ሲያስቆጥሩ÷ የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ ግብ ደግሞ ፍጹም ጥላሁን ከመረብ አሳርፏል፡፡