አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ደሃና ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
ከእብና ከተማ ወደ ሰቆጣ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በደሃና ወረዳ ቀበሌ 9 ድግሽዋ ተብሎ በሚጠራ ሥፍራ የትራፊክ አደጋ እንደደረሰበት ተገልጿል፡፡
በተከሰተው አደጋም የ18 ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ÷ 62 ሰዎች ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በደሃና ወረዳ አምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት እየተሰጣቸው መሆኑን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት መረጃ አመልክቷል፡፡