አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና ከእሑድ ኤአይ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) የሙዚቃ ውድድር አካሂደዋል።
በዚህም በውድድሩ ከቀረቡ ስራዎች መካከል ምርጥ 20 ሙዚቃዎች መለየታቸውን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል።
በውድድሩ ከ600 በላይ ተወዳዳሪዎች ሥራዎቻቸውን ያስገቡ ሲሆን÷ ምርጥ 20ዎቹ በትናንትናው ዕለት ተለይተዋል።
ለውድድሩ አሸናፊዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።
ውድድሩ ተወዳዳሪዎች ያላቸውን አቅም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ታግዘው ለአድማጭና ተመልካቾች ሙዚቃ የሚያቀርቡበትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ተመላክቷል።
ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ እንዲያድግና ጥልቅ የሆኑ የሳይንሳዊ ምርምር ስራዎችን በመስራት የሕብረተሰቡን ችግር በቴክኖሎጂ ለመፍታት ግብ ይዞ እየሰራ ይገኛል።