የሀገር ውስጥ ዜና

የመስኖ እርሻ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የጸና መሰረት የጣልንበት ምዕራፍ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

April 28, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የበጋ መስኖ እርሻ፤ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሰረትን የጣልንበት ምዕራፍ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ የበጋ መስኖ እርሻ፤ በምግብ ራሳችንን ለመቻል በሚደረገው ጉዞ ውስጥ የጸና መሰረትን የጣልንበት ምዕራፍ ነው ብለዋል።

የውሃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እንደሚያሸጋግረን ጥርጥር የለውም ሲሉም አመልክተዋል።