ፋና ስብስብ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞ አፈ ጉባኤ ያለው አባተ ሥርዓተ ቀብር ነገ ይፈጸማል

By Adimasu Aragawu

April 28, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞ አፈ ጉባኤ አምባሳደር ያለው አባተ ሥርዓተ ቀብር በነገው ዕለት ይፈጸማል።

ምክር ቤቱ ለፋና ዲጂታል እንደገለጸው፤ የቀድሞ አፈ ጉባኤ አምባሳደር ያለው አባተ ክብራቸውን የሚመጥን ሥርዓተ ቀብር ለማስፈጸም ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሰራ ይገኛል።

በመሆኑም በነገው ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው በማርች ባንድ የታጀበ የአስከሬን ሽኝት ተደርጎ፤ በመንበረ ጸባኦት ቅድስተ ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን ሥርዓተ ቀብሩ ይፈጸማል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞ አፈ ጉባኤ አምባሳደር ያለው አባተ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።