የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት ለነዳጅ በወር 20 ቢሊየን ብር ድጎማ እያደረገ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Hailemaryam Tegegn

April 28, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ወራት ያጋጠመውን ዓለም አቀፍ የነዳጅ ችግር ለመፍታት መንግስት በወር 20 ቢሊየን ብር ድጎማ እያደረገ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ የተለያዩ ሀገራት አየር መንገዶች በረራዎቻቸውን እየቀነሱ ሲሆን፥ ችግሩ በዚሁ ከቀጠለ በረራ እንደሚያቆሙ እየገለጹ ይገኛሉ ነው ያሉት፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ እንዳላቋረጠ እንዲሁም የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዳልቆመ ገልጸው፥ ነገር ግን አንድም ኢትዮጵያዊ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ብሎ ሲጠይቅ አልተስተዋለም ብለዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት ገደማ ለነዳጅ ተጨማሪ ወጪ 100 ፐርሰንት ድጎማ መደረጉን ገልጸው፥ በዚህም በወር እስከ 20 ቢሊየን ብር ድጎማ እያደረግን እንገኛለን ነው ያሉት፡፡

በኃይለማርያም ተገኝ