አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ነገሌ አርሲ እና ፋሲል ከነማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ወጥተዋል፡፡
በዚሁ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
አስቀድሞ ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ መቐለ 70 እንደርታ እና ሀድያ ሆሳዕና 1 አቻ መለያታቸው ይታወቃል፡፡
በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 10 ላይ መደረግ የጀመረው የአርባ ምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ቀጥሏል፡፡