አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ አድራጎት የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ዱባይ፣ ኒውዮርክ፣ ቤጂንግ እና ናይሮቢ ሲካሄድ ቆይቶ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
ሩጫው ከመስቀል አደባባይ መነሻውን አድርጎ በለገሃር መብራት፣ በብሔራዊ ቴአትር መብራት አድርጎ የቀድሞው ኢቢሲ መብራት ላይ ዞሮ በሠንጋ ተራ መብራት፣ በሜክሲኮ አደባባይ፣ በቡናና ሻይ ለገሀር በማድረግ ፍጻሜው መስቀል አደባባይ ይሆናል።
ይህ የጎዳና ላይ ሩጫ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
በዚህም መሠረት፦
👉 ከቅዱስ ዑራኤል ወደ መስቀል አደባባይ (ባምቢስ ወይም መቅረዝ ሆስፒታል ላይ)
👉 ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
👉 ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ጥላሁን አደባባይ ላይ)
👉ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ለገሀር መብራት ላይ)
👉 ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ላይ)
👉 ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ)
👉ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛ ላይ) ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የሩጫ ፕሮግራሙ እስኪጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።
በተጨማሪም ለፕሮግራም ሲባል ከዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በመስመሮቹ ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
ሕብረተሰቡ ማንኛውም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በነጻ የስልክ መስመሮች 990፣ 991፣ 987፣ 816 እንዲሁም በ011-1-26-43-59፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ መስጠት እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል።