የሀገር ውስጥ ዜና

ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የፓን አፍሪካ ፓርላማ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

By Adimasu Aragawu

May 01, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የፓን አፍሪካ ፓርላማ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር አሸብር የፓን አፍሪካ ፓርላማ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን የምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል።

ምክር ቤቱ በዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ መመረጥ የተሰማውን ደስታ በመግለጽ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸውም ተመኝቷል።