አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲሱ የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና አስተዳደር ሥርዓት በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ነው አሉ የብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን።
አምባሳደር ሬድዋን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባባር ያለማውን የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና አስተዳደር ሥርዓት ቴክኖሎጂን ባስመረቀበት ወቅት ነው ይህንን የገለጹት።
በዚሁም ሥርዓቱ ከዚህ በፊት የነበሩ የአሰራር ሂደቶችን በማረቅ በማስረጃ ላይ የተመሠረተ ሕጋዊ ተጠያቂነት የሚያሰፍን እንደሆነ ተናግረዋል።
ግልፅና የዜጎች ተሳትፎ የሚረጋገጥበት መሆኑን በማንሳትም የጋራ መግባባትን በመፍጠር በሚዲያው እና በተቆጣጣሪ ቋማት መካከል ያለውን ግንኙነት እንደሚያሳድግ አስረድተዋል።
የቴክኖሎጂ ሥርዓቱ በዘርፉ የነበረውን የአሰራር መጓተት በማስተካከል የዲጂታል ሥርዓትን የሚያረጋግጥ እንደሆነም አብራርተዋል።
በወንድሙ አዱኛ