የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ጎበዝ ሶላር ሴል ማምረቻን ጎበኙ

By Melaku Gedif

May 02, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ በሁዋጂያን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ የሚገኘውን “ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት÷ ይህ ፋብሪካ በ2025 ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያድርጉ ፎረም አማካኝነት በተፈረመው ስምምነት መነሻ በ100 ሚሊየን ዶላር የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የተቋቋመ ነው።

‎በውጤታማ ድጋፍ እና ክትትል በስድስት ወራት ብቻ እውን የሆነው “ጎበዝ ሶላር ሴል” ማምረቻ በዘመናዊ ማሽኖች እና ቴክኖሎጂ የተዋቀረ መሆኑን ጠቁመዋል።

ማምረቻው ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ፈጥሯልም ነው ያሉት።

‎በመጀመሪያ ምዕራፍ 2 ጊጋዋት ዓመታዊ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካው የኢትዮጵያን የኃይል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ከታዳሽ ኃይል ለማድረግ ለተጀመረው ሀገራዊ ርዕይ እውን ለማድረግ ተደማሪ አቅም ፈጥሯል ብለዋል።