አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፔክስ የመንገደኞች ምርጫ የ2026 የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ በመባል ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
ሽልማቱ አየር መንገዱ የተሳለጠ፣ ምቹና አስተማማኝ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለማቅረብ ያለውን ያልተቋረጠ ትጋት የሚያሳይ ሲሆን፥ በአቪዬሽን አገልግሎት ዘርፉ ያለውን መሪነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ነው የተገለጸው፡፡
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት እንዳሉት፥ እውቅናው የአየር መንገዱ ሰራተኞችና አመራሮች ትጋት ውጤት ነው፡፡
ሽልማቱ በደንበኞች ምርጫ መሰረት የተሰጠ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸው፥ የአገልግሎት ደረጃዎቻችንን እንድናሳድግና በደንበኞቻችን የተጣለብንን እምነት እንድንጠብቅ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል፡፡