አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት የሚከበረውን 85ኛውን የአርበኞች መታሰቢያ ቀን ምክንያት በማድረግ መድፍ ይተኮሳል አለ የመከላከያ ሚኒስቴር።
በዚህ መሰረትም ነገ ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡
ስለሆነም የመዲናዋ ነዋሪዎች በጉዳዩ ላይ ተገቢው መረጃ እንዲኖራቸው ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል፡፡