የሀገር ውስጥ ዜና

የክብር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

By Mikias Ayele

May 05, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ስድስት ኪሎ የተገነባው የክብር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመርቋል።

የመታሰቢያ ሐውልቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ መርቀዋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም አርቲስቶች ተገኝተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዓመታት እየተሰሩ ካሉ የኮሪደር ልማት እና የወንዝ ዳርቻ እንዲሁም ከተማዋን የማስዋብ ተግባር ታሪክን፣ ጥበብን እና አጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ማንነትን የሚዘክሩ ሐውልቶች አብረው እየቆሙ መሆኑ ይታወቃል።

በተለይም በኢትዮጵያ ሥነጽሁፍ ውስጥ ጉልህ አሻራቸውን ያሳረፉት ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን እና ደራሲ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የመታሰቢያ ሐውልት እንደቆመላቸው ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ የሙዚቃ ንጉሱ የክብር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት በይፋ ተመርቋል።

በዙፋን ካሳሁን