የሀገር ውስጥ ዜና

ጥበብ ሀገር ትሠራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Mikias Ayele

May 05, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥበብ ሀገር ትሠራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች አሉ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሀገር ባለውለታ ለሆኑና በጥበብ ሙያቸው ለኢትዮጵያ ሀገራችን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በከተማችን አዲስ አበባ የመታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸዋል ብለዋል።

በመልዕክታቸውም ጥበብ ሀገር ትሠራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች ነው ያሉት።