አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ30ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሁለቱንም ግቦች ናትናኤል ዳንኤል አስቆጥሯል።
የሊጉ መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ ቀን 10 ሰዓት ላይ በዚሁ ስታዲየም መቐለ 70 እንደርታ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን እያደረጉ ሲሆን÷ በተመሳሳይ ስታዲየም ምድረ ገነት ሽረ እና ባህር ዳር ከተማ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።