ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሩሲያ እና ዩክሬን የተናጥል የተኩስ አቁም ስምምነት አወጁ

By Adimasu Aragawu

May 05, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ እና ዩክሬን የቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት በናዚ ጀርመን ላይ ድል የተቀዳጀችበትን ቀን ለማክበር የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ስምምነት አውጀዋል።

ሩሲያ በፈረንጆቹ ግንቦት 8 እና 9 የተኩስ አቁም እንደምታደርግ የገለጸች ሲሆን÷ ዩክሬን ይህንን ስምምነትን ከጣሰች በማዕከላዊ ኪየቭ ላይ መጠነ ሰፊ የሚሳኤል ጥቃት እንደምታደርግ አስታውቃለች።

ዩክሬን በበኩሏ÷ ከፈረንጆቹ ግንቦት 6 እኩለ ሌሊት ጀምሮ የተኩስ አቁም እንደምታደረግ ገልጻለች።

ይህ የሚሆነው ግን ሩሲያም የተኩስ ጥቃት ማድረሷን ካቆመች ነው ማለቷን ቢቢሲ ዘግቧል።

ሁለቱ ሀገራት የአንድ ወገን የተኩስ አቁም ስምምነት ማወጃቸውን ቢገልጹም በውል፣ በጊዜ ገደብ እና በሌሎች ነጥቦች የጋራ ስምምነት ላይ አልደረሱም።

ለሀገራቱ የተኩስ አቁም ስምምነት ምክንያት የሆነው የቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት በ2ኛው የዓለም ጦርነት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችው ድል በየዓመቱ በፈረንጆቹ ግንቦት 9 በሩሲያ እና በአንዳንድ የቀድሞ የሶቪየት ሕብረት ሀገራት በታላቅ ድምቀት ይከበራል።

በብርሃኑ አበራ