የሀገር ውስጥ ዜና

የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የጀመርነው ጥረት በላቀ ውጤት ቀጥሏል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

By Melaku Gedif

May 06, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የጀመርነው ጥረት በላቀ ውጤት ቀጥሏል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷‎ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱልልታ ወረዳ በ2 ሺህ 150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ማሳን ተዘዋውረን ተመልክተናል ብለዋል።

የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የጀመርነው ጥረት በላቀ ውጤት ቀጥሏል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡