የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ተወያዩ

By Hailemaryam Tegegn

May 06, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር በስልክ ተወያይተዋል። ‎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠናል ነው ያሉት።