ዓለምአቀፋዊ ዜና

ለኢራን የሲቪል ኑክሌር ኢነርጂ ልማት የቻይና ድጋፍ

By abel neway

May 06, 2026

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍኤምሲ) የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ለኢራን የሲቪል ኑክሌር ኢነርጂ ልማት ያላትን ድጋፍ ታስቀጥላለች አሉ።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኢራን አቻቸው አባስ አራግቺ ጋር በቤጂንግ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት ዋንግ ዪ እንዳሉት፤ ቻይና ኢራን ወታደራዊ ኑክሌርን መሳሪያ ላለማልማት ያላትን ቁርጠኝነት ቻይና ታደንቃለች።

ኢራን ለሰላማዊ አገልግሎት የሚውል የኑክሌር ኢነርጂ ልማት የማከናወን መብት እንዳላት ጠቅሰው፤ ለዚህም ቻይና ድጋፏን ትቀጥላለች ብለዋል።

እንደ ኒውስዊክ ዘገባ፤ የአሜሪካ/እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጀምሮ ዋንግ ዪ እና አራግቺ ሰላምን ማስፈን ስለሚቻልበት ሁኔታ ቢያንስ ሶስት ጊዜ ያህል በስልክ ተወያይተዋል።

ከጦርነቱ ወዲህ በአካል ተገናኝተው ሲነጋገሩ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ባለፈው ሰኔ በተካሄደው ዘመቻ እና አሁን በቅርቡ በነበረው ጦርነት የኢራን ብዙዎቹ የኑክሌር ጣቢያዎች ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።