አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍኤምሲ) ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፈው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሳድ ሶዚ (ቴንጌ ቴንጌ) የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
በቲክ ቶክ ልዩ የዳንስ እና አክሮባቲክስ ስራዎቹ ዓለም አቀፍ ዝናን የተጎናጸፈው ዩጋንዳዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቴንጌ ቴንጌ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እውቅናውን ለማህበራዊ አገልግሎት እያዋለ ይገኛል፡፡
“ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ” በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።
የተጽዕኖ ፈጣዎቹ ጉባኤ የአፍሪካን ልዩ ታሪክ ከማስተዋወቅም ባለፈ የአፍሪካ ሀገራትን ትብብር ለማጠናከር እና የአህጉሪቱን ገጽታ በትክክል ለማስተዋወቅ እንደሚረዳ ተነግሯል፡፡
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ እና ኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ በመተባበር ያዘጋጁት የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።